ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር ሦስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።
በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት ሦስት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሦስተኛውን ሽልማት ከማሌዢያ፣ ሜክሲኮ እና ኬንያ ቡድኖች ጋር ተጋርተዋል።
ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሦስት የውድድር ትራኮች ተከፋፍሎ የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውድድሩ ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ሚኒስቴሩ የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ተሳትፎውን በማሳደግ ከዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ÷ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
FBC
More Stories
እንደ አዕዋፍ በሰማይ የሚበርር፣ እንደ ዓሣ በባሕር የሚዋኝ ዓለምን ያስገረመው አስደናቂው “ስካይ ኤክስ” ቴክኖሎጂ
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ