በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡
በክረምቱ አዳዲስ አሰልጣኞችን የሾሙት ሁለቱ ክለቦች የውድድር ዓመቱን በድል ለመጀመር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ቼልሲ ከሪያል ማድሪድ የተሰናበተውን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ እንዲሁም ፉልሃም በተመሳሳይ ሪያል ማድሪድን በጊዜያዊነት ሲያሰለጥን የነበረውን አልቫሮ አርቤሎዋን በዚህ ክረምት መሾማቸው ይታወሳል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በክራቨን ኮቴጅ የሚደረገውን የምዕራብ ለንደን ደርቢ የ36 ዓመቱ ጆን ብሩክስ በመሃል ዳኝነት ይመሩታል፡፡
ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ቦርንማውዝን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ 2 አቻ መለያየቱ ይታወቃል፡፡
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል