ዲዬጎ ማራዶና በ1986 የሜክሲኮ ዓለም ዋንጫ እንግሊዝን 2 ለ 1 ባሸነፉበት ጨዋታ “የፈጣሪ እጅ” እና “የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ግብ” ያስቆጠረበት አዲዳስ አዝቴካ ኳስ በጨረታ ተሸጧል።
ምንም እንኳን ጨረታው እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ተብሎ ቢገመትም በመጨረሻ ግን በ3 ነጥብ 35 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ ችሏል።
ይህ ታሪካዊ ኳስ ቀደም ሲል የጨዋታው ዋና ዳኛ ለነበሩት ቱኒዚያዊው አሊ ቢን ናሰር የተሰጠ ሲሆን፣ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የጨረታ መድረኮች ላይ ሲቀርብ ቆይቶ አሁን ላይ አዲስ ባለቤት አግኝቷል።
የ39 ዓመት ታሪክ ያለው ይህ ኳስ በገበያ ላይ የ3 ነጥብ 35 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ቢያወጣም ለ40 ሚሊዮን አርጀንቲናውያን ግን በገንዘብ የማይመነዘር የክብር ምልክታቸው ነው፡፡
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል