ግዝፈቱና ውበቱ ብዙዎችን ያስደመመው የደቡብ ኮሪያው ሺንሴጌ ሴንተም ሲቲ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የዓለማችን ግዙፉ የገበያ ማዕከል ሆኖ ተመዝግቧል።
በደቡብ ኮሪያ “ቡሳን” ከተማ የሚገኘው ይህ አስደናቂ የሕንፃ ጥበብ ውጤት ለገበያ ብቻ ሳይሆን ለመዝናኛም ተመራጭ ስፍራ ሆኗል።
ማዕከሉ በ16 ፎቆች ላይ ያረፉ 700 የሚጠጉ ሱቆችን የያዘ ሲሆን ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ታዋቂ ብራንዶችን በአንድ ጣራ ስር ያገናኛል።
በውስጡም የበረዶ ላይ መንሸራተቻ፣ የጎልፍ መለማመጃ፣ ስፓ፣ ዘመናዊ ሲኒማ ቤቶችና ግዙፍ የምግብ አዳራሾችን አካቷል።
ይህ የገበያ ማዕከል በቀን በአማካይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ጎብኝዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን፣ ለደቡብ ኮሪያ የቱሪዝም ዘርፍም ከፍተኛ ገቢ እያስገኘ እንደሚገኝ ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
More Stories
ዓለምን ያስደመመው ኢትዮጵያዊ ዲዛይነር
ኢራን በአሜሪካ እና እስራኤል ላይ ከእስካሁኑ የከፋ “አውዳሚ” ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል አስጠነቀቀች።
የተደበቁ ሀብቶች በአደባባይ፡ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አዳዲስ የቱሪዝም ገጽታዎች