የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተመዘገቡ የግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጀውን የነፃ የአየር ሰዓት ድልድል ይፋ አድርጓል።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ምርጫውን በጊዜ ሰሌዳው መሠረት ለማካሄድ ቦርዱ ልዩ ልዩ የቅድመ-ምርጫ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
የግል ዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ሕጉን ተከተለውና በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ የምርጫ የሕግ ማዕቀፎችን፣ የኦፕሬሽን ሥራዎችን እና የቅስቀሳ ሥነ-ምግባርን በተመለከተ በቦርዱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሕግ ባለሙያዎች ዝርዝር ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የወጣው የነፃ የአየር ሰዓት ድልድል ለወንድ የግል ዕጩዎች እያንዳንዳቸው በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ እና በጋዜጣ የ15 ደቂቃ ዕድል ይሰጣል።
ሴት እና አካል ጉዳተኛ ዕጩዎችን ለማበረታታት ደግሞ ቦርዱ ልዩ ድልድል አድርጓል። በዚህም መሠረት ሴት ዕጩዎች አንድ ተጨማሪ ዕድል፣ ወንድ አካል ጉዳተኞች አንድ ተጨማሪ ዕድል፣ እንዲሁም ሴት አካል ጉዳተኛ ዕጩዎች እስከ አምስት የሚደርስ ተጨማሪ የአየር ሰዓት ዕድል እንዲያገኙ ተወስኗል።
በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቦርዱ አመራር አባላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።