በተለያዬ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነጋዴዎችና ሌሎች ግብር ከፋዮች ወቅቱን የጠበቀ ገቢ ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመረዳት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የማሻ ከተማ ገቢዮች ቅርጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በተለይ ደረሰኝ መስጠትና ጠይቆ ከመቀበል አንጻር የሚስተዋሉ ችግሮች ልቀረፉ እንደሚገባም ጽ/ቤቱ አሳስቧል ።
የገቢ ዕድገትን ለማረጋገጥ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት እና በጋራ መስራት ለነገ የሚባል አይደለም የሚሉት አቶ ዳንኤል ገ/እግዚአብሔር የማሻ ከተማ ነዋሪና በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ስሆን ገቢ ለሀገር እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው የሚጠበቅባቸውን በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በጸጉር ስራ ላይ የተሰማራው ወጣት መብራተ ዱሎ በበኩሉ የከተማው ዕድገት እንዲፋጠን ሁሉም የየራሱን የዘግነት ግደታ መወጣት አለበት ብለው ተቋሙ ደግሞ በገቢ ግመታ ወቅት ቅረታ ስቀርብ በቂ ምላሽ ልሰጥ አንደሚገባ አንስተዋል።
ግብር በወቅቱ ከተከፈለ ዕዳ አለመሆኑን በመረዳት ሁሉም ከሚያገኘው ገቢ መክፈል አለባቸው የሚሉት አስተያዬት ሰጭዎቹ የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ የህዝቡን ፍላጎት በመረዳት ምላሽ ልሰጥ ይገባል ብለዋል።
ለአንድ አካባቢ የኢኮኖሚ ዕድገትና ለህብረተሰቡ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠት የገቢ አሰባሳቢ ስርዓትን ማዘመን ወሳኝ መሆኑን ያነሱት የማሻ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሣሙኤል ገቦ በዚህ መነሻ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የ8ወር አፈጻጸም ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ 75 .2 በመቶ ብቻ የተሰበሰበ በመሆኑ የከተማው ግብር ከፋዮች ቅጣት ውስጥ ሳይገቡ ፈጥነው የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡም ጥሪ ያቀረቡት ኃላፊው ግብር ከፋው ህብረተሰብ በአድሱ ግብር መክፈያ መመሪያ መሠረት መክፈል እንደሚገባና በዚህ ወቅት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ተቋሙ መርምሮ ምላሽ እንደሚሰጥና ከዚህን መሠል ተግባራት ስከናወኑ እንደ ነበር አስታውሰዋል።
በተለይ ደረጃ ”ሀ” ግብር ከፋዩ ደረሰኝ ቆርጦ ያለመስጠት በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ጠቁመው ሸማቹ ህብረተሰብም የሚሰበሰበው ገቢ የራሱ መሆኑን በመረዳት ደረሰኝ እንዲቀበልና ከገቢ አዋጅ ውጭ በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።
ግብር ከፋዮች ወቅቱን የጠበቀ ገቢ ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ…
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።