በመካከለኛው ምሥራቅ እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን ጋር እያካሄዱት የሚገኘው ጦርነት አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የቀጣናው ጦርነት በተለይም የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦትን በማስተጓጎል የሀገራት ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደረ ይገኛል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው ዕለት በአሜሪካና ኢራን መካከል ንግግር መጀመሩን ይፋ አድርገው ነበር፤ በአንጻሩ ኢራን የፕሬዚዳንቱን ሃሳብ ሐሰተኛ መረጃ ስትል አስተባብላለች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን የኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን÷ ቴህራንም የአጸፋ ርምጃ መውሰድ ጀምራለች፡፡
በንግግር ዙሪያ ሀገራቱ የሚያሰራጩትን እርሰ በርሱ የሚጣርስ መረጃ እና አዲስ ጥቃት መከፈቱን ተከትሎም ቋፍ ላይ የነበረው የነዳጅ ዋጋ በድጋሚ ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡
በዚህም መሰረት ከ10 በመቶ በላይ ቅናሽ አሳይቶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት መሸጫ ዋጋ በዛሬው ዕለት ከ100 ዶላር በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በእስያ ሀገራት የነዳጅ ዘይት አቅርቦት እጥረት በስፋት የተስተዋለ ሲሆን÷ የዋጋ ጭማሪ እያሳየ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ፍላጎት አለማሳየቷና እስራኤልና አሜሪካ በኢራን የሃይል መሰረተ ልማቶች አዲስ ጥቃት መጀመራቸውም ችግሩን ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡
25ኛ ቀኑን ያስቆጠረው ጦርነት በነዳጅ ዘይት አቅርቦት ላይ እያስከተለ ያለውን ጫና ለመቋቋም ሀገራት የተለያዩ የመፍትሔ ርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጠረው የነዳጅ አቅርቦት ችግር በርካታ ሀገራት ታዳሽ የኃይል አማራጭን ይበልጥ እንዲያጠክሩ እድል መፍጠሩ ተመላክቷል፡፡
More Stories
እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን የኢነርጂ መሰረተ ልማት ላይ ጥቃት ፈጸሙ
ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲ ዕጩዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል ለመወሠን የሚያስችለውን የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በይፋ አስጀመረ
በኢራን ጉዳይ ቻይና ጥሪ አቀረበች