የሸካ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አረጋኽኝ አለሙ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ሠላም በር ቀበሌ በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በጀት ድጋፍ የተሰሩ ስራዎች የመስክ በዓል (Field Day) ልምድ ልውውጥ ተካሂዷል።
በሠላም በር ቀበሌ ዲካይ መንደር በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) በጀት ድጋፍ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የተሰራውን የዓሳ ኩሬ የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።
የሸካ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አረጋኽኝ አለሙ በመስክ ምልከታው ላይ ባደረጉት ንግግር የዓሳ እርባታ ስራ እንደ ዞን በማሻ ማረምያ ቤት ጥሩ ውጤት የታየበት መሆኑን አስታውሰው ነገር ግን እንደ የኪ ወረዳ ሲሰራ የመጀመሪያው ሲሆን ተግባሩ የሌማት ትሩፋት አካል በማድረግ በመስክ ምልከታው የተሳተፉ የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ሞዴል አርሶ አደሮች ያገኙትን ልምድ ወደየ ቀበሌዎቻቸው ሊያሰፉ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሠላም በር ቀበሌ ችግኝ ጥቢያ ውስጥ የሚገኝ ዘመናዊና በምርት አሰጣጡ የተሻሻለ ግራፍት ለማድረግ በዝግጅት ላይ የሚገኝ የአቦካዶ ችግኝ፣ የፈሰሰ የቡና ዘር፣የከብት መኖ ሳር ችግኝ፣በሰላም በር ቀበሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የሚገኝ ጥምር እርሻ የመስክ ልምድ ልውውጥ ተካሂዷል።
በመስክ ልምድ ልውውጡ የተሳተፉ አካላት በሰጡት አስተያየት ከልምድ ልውውጡ ብዙ ግብአት ማግኝታቸውን ገልፀው ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር ወደየ ቀበሌዎቻቸው እንደሚያሰፉ ተናግረዋል።
የሸካ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አረጋኽኝ አለሙ ፣የሸካ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ በዛብህ፣ የየኪ ወረዳ ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ሽብሩ አንጉሎ፣የቀበሌ አስተዳዳሪዎችና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ሞዴል አርሶ አደሮች በመስክ ልምድ ልውውጥ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል ሲል የወረዳው መ/ኮ/ጉ ዘግቧል።
More Stories
የኢራን አዲሱ መንፈሳዊ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ …
የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤትነት ጥያቄ ለቀጣናዊ ሰላም ያለው ፋይዳ
የኮንታ ዞን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በአመያ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።