ማሻ፤ የካቲት 20/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከባለሃብቶች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ክልላዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በሚዛን አማን ከተማ ተካሂዷል።
መድረኩ በኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በተደራጀ መንገድ ለመፍታትና የክልሉን የኢንቨስትመንት ፍሰት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል።
የፎረሙን ማጠቃለያ መድረክ የመሩት የክልሉ ርዕሰመስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ያደጉ ሀገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ያስመዘገቡት በግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ታግዘው መሆኑን ተናግረዋል።
የኢንቨስትመንት መሠረተ ልማት ችግሮችን ለመፍታት በትብብር መስራት እንደሚገባ የገለጹት ርዕሰመስተዳድሩ ከአገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የማያዳግም እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ተናግረዋል።
የግሉ ዘርፍ የፈጠረውን አቅም በመጠቀም ገበያ ተኮር ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም የተናገሩት ዶክተር ነጋሽ የክልሉ መንግስት ለተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ዕድገት ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የግል ባለሀብቶች ከመደበኛው ኢንቨስትንነት ስራ ጎንለጎን የአካባቢውን ማህበረሰብ በተለያዩ ዘርፎች ማገልገል እንዳለባቸውም ርዕሰመስዳደድሩ ገልጸዋል።
የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ የኢንቨስትመንት ዘርፉን በማስፋት ክልሉን ተቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የመንግስት ትኩረት መስኮችን በመለየትና ከግሉ ባለሀብት የሚነሱ አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በቅንጅት ለመፍታት ያለመ መሆኑንም አቶ ታሪኩ ገልጸዋል።
የፎረሙ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በኢንቨስትመንት ዘርፉ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በተደራጀ መንገድ ለመፍታትና የክልሉን የኢንቨስትመንት አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
#SWMN
ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ዕድገት ማነቆ የሚሆኑ ችግሮች ተለይተው በዘላቂነት መፈታት አለባቸው፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።