ማሻ፤ የካቲት 18/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአሜሪካ የምስራቅ የባህር ዳርቻ ላይ በረዶ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ በመከሰቱ ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰርዘዋል፡፡
በዚህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች እንግልት ሲያጋጥማቸው ከ5 ሺህ በላይ በረራዎች መሰረዛቸው ተመላክቷል፡፡
በሮድ አይላንድ እና በማሳቹሴትስ 37 ኢንች የሚጠጋ የበረዶ ዝናብ የተመዘገበ ሲሆን በኒውዮርክ ከተማ ሴንትራል ፓርክ ደግሞ ከ19 ኢንች በላይ የበረዶ ግግር መገኘቱን የብሔራዊ አየር ሁኔታ አገልግሎት መግለጹን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ትንሹ የአሜሪካ ግዛት ሮድ አይላንድ የከፋ በረዶ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ያጋጠመው አካባቢ መሆኑን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን መዘገባቸው ተጠቁሟል፡፡
በአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ላይ የኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ማጋጠሙም ተገልጿል።
በአካባቢው ውስጥ የሚደረገው ጉዞ የተገደበ ሲሆን አንዳንድ ግዛቶች እና ከተሞች የጉዞ እገዳን በመተግበር ላይ መሆናቸው ነው የተመላከተው፡፡
የበረዶ ክምችቱ በሰሜን ምስራቅ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ከ30 እስከ 61 ሴ.ሜ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ያጋጠመው በረዶ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ክስተት እስከ ቀጣይ ሰኞ ድረስ ሊቆይ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
More Stories
የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ዳግም ያረጋገጡ አዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች…
በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ ተጠቃሚ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ ዝናብ ያገኛሉ ተባለ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ