ማሻ፤ የካቲት 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የዘመናችን የዕውቀትና የሥራ ዓርበኞች ከፍ ያለውን ኢትዮጵያዊ ርዕይን ለማሻገር የትናንቱን የመስዋዕትነት ችቦ በሥራ ወዳድነት አስቀጥሉት ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አስገነዘቡ።
ፕሬዚዳንት ታዬ ለ89ኛው የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም ይህ መታሰቢያ ኢትዮጵያን ማፍቀርና መውደድ፤ ለኢትዮጵያ ራስን ፈጽሞ መስጠት ምንጊዜም የማይጠፋ የሐሳብ እቶን እና የማይበርድ የመንፈስ ሙቀት መሆኑን ያስመሰከርንበት ነው ብለዋል።
ራስን ለታላቅ ሀገራዊ ርዕይ አሳልፎ መስጠቱ በኢትዮጵያ የነበረ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ለአንድነቷና ለዕድገቷ በሚተጉ ዜጎቿ ዛሬም ሲገለጥ የምናየው ነገም በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ፀንቶ የሚኖር ህያው ኃይል እና የማያቋርጥ ጥሪ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የዘመናችን የዕውቀትና የሥራ ዓርበኞች ከፍ ያለውን ኢትዮጵያዊ ርዕይና ተስፋችንን ለማሻገር የትናንቱን የመስዋዕትነት ችቦ በጥበብ ፈላጊነት እና በሥራ ወዳድነት አስቀጥሉት ሲሉም አስገንዝበዋል በመልዕክታቸው።(ኢዜአ)
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ