ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሦስት አዳዲስ የሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማሪፊያዎች በሚያዚያ ወር ተመርቀው ስራ ይጀምራሉ አለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ።
አየር መንገዱ ባወጣው መረጃ÷ በግንባታ ላይ ከሚገኙት የሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማሪፊያዎች መካከል በመጪው ሚያዚያ ወር ሦስቱን በማስመረቅ በረራ ለመጀመር ማቀዱን አስታውቋል።
እነዚህ አዳዲስ መዳረሻዎች ነገሌ ቦረና፣ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ መሆናቸውንም አመልክቷል።
#ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።