ማሻ፤ የካቲት 9/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በሰሜናዊ ናይጀሪያ ሞተር ሳይክል በመጠቀም በተፈጸመው የታጣቂዎች ጥቃት 46 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ጥቃቱ በሦስት የተለያዩ መንደሮች ውስጥ የተፈጸመ ሲሆን፥ ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአልጀዚራ ዘገባ ያመላክታል።
በኒጀር ግዛት የተፈጸመው ጥቃት ከአሸባሪው አይ ኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ እና ሰዎችን በማገት ገንዘብ የሚጠይቁ ታጣቂዎች አማካኝነት ሳይፈጸም እንደማይቀርም ዘገባው አመላክቷል።
በጥቃቱ በርካታ መኖሪያ ቤቶችም በእሳት የተቃጠሉ ሲሆን፥ እስካሁን ያልተለየ አስከሬን መኖሩንም ባለስልጣናቱ ገልጸዋል።
በሰሜናዊ ናይጀሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ መጥተዋል።
#አራዳ ኤፍ ኤም
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።