ማሻ፤ የካቲት 3/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የዓለም አትሌቲክስ የውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ግብዣ መሰረት ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዳይሬክተሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በዓለም አትሌቲክስ እውቅና ያገኘውን የአደይ አበባ ዓለም አቀፍ የመለማመጃ ትራክ ስቴዲየም እና የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚን ጎብኝተዋል።
የዳይሬክተሩ ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣይ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን፣ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ እንዲሁም አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል።
ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ስፖርት ዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
ፒርስ ኦክላጋን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ መሀመድ፣ ከፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን እና ከፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሰረተ ልማት እና በውድድር ዝግጅቶች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል