ማሻ፤ የካቲት 2/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ መንግስት በጀት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን የባቹማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።
የኮሌጁ ግንባታ በ2011 ዓ/ም በቀድሞው የደቡብ ክልል ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የተቋረጠ ሲሆን፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት በ2017 ዓ/ም ውሉን እንደገና በማሳደስ ግንባታውን በድጋሚ በማስጀመር ቅርብ ድጋፍና ክትትል በማጠናከር በአንድ ዓመት ውስጥ ግንባታውን አጠናቅቆ ለምረቃ አብቅቷል።
በመርሐግብሩ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ፣ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መ/ኮ ነው
More Stories
ለ7ኛዉ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በአንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ ተካሂደዋል ።
ጋዜጠኞች ሙያቸውን እና ሕግን እንዴት መከተል እንዳለባቸው ሊያውቁ ይገባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።