ማሻ፤ ጥር 14/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2018 ዓ.ም የበልግና የተፋሰስ ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል ።
በማጠቃለያው አስተያየት የሰጡት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በክልሉ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም የተሻለ ዕድገት ማስመዝገብ ይገባል ብለዋል።
የገጠር የግብርና ሽግግር የአርሶና አርብቶ አደሩን ኑሮ ለመቀየር እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግዳሮት ሆኖ የነበረውን የግብርና ዘርፍ የፋይናንስ ብድር አሁን ላይ መንግስት ማመቻቸቱ እመርታዊ ለዉጥ መሆኑን ተናግረዋል ።
በስራዉ የግብርና ሽግግር የገጠር ሽግግር ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።
በግብአት አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች መኖራቸዉን ገልፀዉ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዉ በዘርፉ ዩንየኖች የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በግብርና ዘርፍ አርሶ አደሩን ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለዉጦችን ማስመዝገብ እንደሚገባ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሚታረስ ማሳ ሽፋንን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የገጠር እና የከተማ ኮልደር ስራ ላይ በተጠናከረ ሁነታ ማስፋፋት፤የመሶብ አገለግሎት ፤የማህበረተሰብ አቀፍ ጤና መድህን፤የፋይዳ መታወቂያ እና ለሎች ኢንሼቲቭቦች በተጠናከረ ሁነታ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ በበኩላቸው የ2ዐ18-19 የበልግ ልማት ስራ እና የተፋሰስ ስራን ለማሳካት የሁሉም ርብርብ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል ።
የዘንድሮ በልግ ስራን በተለያዩ አኳሃን መምራት እንደሚገባ ጠቁመዉ ለዚህም በገጠር ትራንስፎርሜሽን ሽግግር ስራዎች እዉን በማድረግ የበልግ ስራን ዉጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በየአመቱ የሚከናወነው የበልግ ስራዎች መሻሻሎች መታየታቸውን የገለጹት አቶ ማስረሻ በዘንድሮ አመት የበልግ ስራ ወደ 5መቶ ሺህ ማሳ በተለያዩ ሰብሎች ማልማት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዓመታዊ የማሳ ሽፋን ከነበረበት 750ሺህ ወደ 1ሚልዮን ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
የማሳ ሽፋን ማስፋፋት ምርት እንደሚጨምር የተናገሩት አቶ ማስረሻ ምርታማነት ለማሳደግ ደግሞ የተለያዩ ግብአቶችን በመጠቀም አማካይ የምርት መጠን ከነበረበት 37ኩንታል በሄክታር ወደ 38 ኩንታል በሄክታር ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህ ደግሞ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል ።
በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም የተሻለ ዕድገት ማስመዝገብ ይገባል፦ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።