ማሻ፤ ጥር 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ቃና ዘገሊላ ከጥምቀት ማግስት በመላ ሀገሪቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል ነው።
በዓሉም ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ አውረጃ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋሪያቱ ጋር በመሆን አንድ ዶክማስ በተሰኘ ሰው ቤት ሠርግ ተጠርተው የታደሙበትና ኢየሱስ ክርስቶስም የመጀመሪያውን ተዓምር ያደረገበት ዕለት ነው።
በዕለቱም በዶክማስ ቤት በርካታ የሠርግ ዕድምተኞች በታደሙበት የድግስ አሳላፊዎች ወይን አልቆባቸው በተጨነቁበት ሰዓት የጭንቅ ደራሿ የድንግል ማርያም ምልጃ የታየበትና የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት መሆኑን የዕምነቱ አስተምህሮ ያስረዳል።
በወቅቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ለአሳላፊዎቹ ስድስቱን ጋኖች በውሃ እንዲሞሉ በማዘዝ ውሃን ወደ ወይን ጠጅ የመለሰበት ዕለትን በማሰብ ምዕመናኑ በድምቀት ያከብሩታል።
ስለበዓሉ ሐይማኖታዊ ዳራ በካፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆኑ በብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ትምህርተ ወንጌል እና ቡራኬ ተሰጥቷል።
በዓሉም በመላ ሀገሪቱ የሊቀ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ባሉበት በተመሳሳይ መልኩ ተከብሮ ውሏል።
የዘንድሮ 2018 ዓመተ ምህረት የቃና ዘገሊላ በዓልም የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ በተገኘበት ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።