February 4, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በክልሉ ለ19 ሺህ ነባር አሽከርካሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በ32 ማዕከላት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁ ተገለጸ

ማሻ፣ ታህሳስ 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በትራንስፖርት ዘርፉ እየተስተዋሉ ያሉትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ የዘርፉ የአገልግሎት እርካታ ኦውን እንዲሆን እንደሚሰሩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

የቢሮ ምክትል ኃላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘመዴ አንዳርጌ እንዳሉት በክልሉ ለ19 ሺህ ነባር አሽከርካሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በ32 ማዕከላት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁን ገልጸዋል።

አክለውም በማህበራትና በመንግስት ተቋማት ሥር የሚሰሩ ነባር አሽከርካሪዎች በተመቻቹ የማሰልጠኛ ማዕከላት ሥልጠናቸውን እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ኃላፊው አሳስበዋል።

የትራንስፖርት ዘርፉ ውስብስብ ችግሮች ያለበት በመሆኑ ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ ተጠናክሮ በርብረብ መሠራት እንዳለበት የጠቆሙት አቶ ዘመዴ የሪፎርም ሥራው ውጤታማ ሆኖ ቀጣይነት እንዲኖረው የዘርፉ አመራሮች በቁርጠኝነት ተግባራቱን መፈጸም የህዝብ ተጠቃሚነት እንዲጨምር ያደርጋል ብለዋል።

የጭነት ትራንስፖርት የትራንስፖርቱ ዘርፍ የጀርባ አጥንት መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘመዴ በዘርፉ ተገቢው መረጃ በማደራጀት የመነሐሪያ ቦታ ልየታ በማድረግ እየተስተዋለ ያለውን ማነቆ መቀነስ እንደሚገባም አሳስበዋል ።

ኃላፊው አክለውም ሁሉም የአሽከርካሪ የማሰልጠኛ ተቋማት የመለማመጃ ሜዳ ሊኖራቸው የግድ ነው ብለው ቀጣይ የአሽከርካሪ መንጃ ፍቃድ የሚሰጣቸው የማሰልጠኛ ሜዳ ላላቸው ብቻ መሆኑን አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተናግረዋል ።

አያይዘውም የተሃድሶ ስልጠናው በመጢው የጥር ወር ውስጥ እንደሚሰጥ አብራርተው በክልሉ ለ19 ሺህ ነባር አሽከርካሪዎች የተሃድሶ ስልጠና በ32 ማዕከላት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁ ገልጸዋል።

በተሳታፊዎች ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት የዘርፉ አመራሮች ሪፎርሙ የትራንስፖርት ዘርፉን ስብራት የጠገነ ከመሆኑ ባሻገር የተገልጋዩን ህብረተሰብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እየቀረፈ የመጣ ቢሆንም አሁን የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመቅረፍ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።