ማሻ ፣ የሰኔ 14፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ፌቨን ጉርጁ ትባላለች በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በ2017 ዓ.ም ከአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች ውስጥ 4 ነጥብ በማምጣት በባሕርዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሳይበር ደህንነት የጥናት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃለች።
ፌቨን ጉርጁ ከ53 ኮርሶች 42ቱን A+ በማምጣትም የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችላለች፡፡
ፌቨን ዩኒቨርሰቲ ከመግባቷ በፊት በነበሩ የትምህርት ደረጃዎች ጥሩ ውጤት እያመጣች እዚህ እንደደረሰች ለኢቢሲ ተናግራለች።
ዩኒቨርስቲ ከገባሁ በኋላም ጥሩ ውጤት አምጥቼ መመረቅ ህልሜ ነበር፤ አሳክቸዋለሁም ትላለች።
ለውጤታማነቴ ከፈጣሪ በታች የቤተሰቦቼ፣ የመምህራኖች ጠንካራ ድጋፍ እና ያደረጉት ጥረት ለውጤት አብቅቶኛል ብላለች።
ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት እውቀት ያላቸው የሰው ሀይል ያስፈልጋታል፤ በዚህም በተመረኩበት መስክ አገለግላለሁ ስትል የወደፊት እቅዷንም ተናግራለች።
ኢቢሲ
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች