ማሻ ፣ የግንቦት 29፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ኢትዮጵያ በለውጡ ዋዜማ 59 በመቶ የሀገር ውስጥ ምርቷ ዕዳ የሆነ እና በቀላሉ በዕዳ የተዘፈቀች ሀገር እንደነበረች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ አውስተዋል።
ዕዳዋን በወቅቱ ያልከፈለች እና አበዳሪ ተቋማት በቀይ ያስቀመጧት ሀገር መሆኗም ብድርም ሆነ ድጋፍ ማግኘት እንዳትችል አድርጓታል ነው ያሉት።
የለውጡ መንግሥት ሥልጣን እንደያዘ ለሠራተኞች ደመወዝ መክፈል የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደነበርም አብራርተዋል።
ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ ቆመው ሕዝቡ “ያስቀመጣችሁትን የመሠረት ድንጋይ ልቀሙልኝ” እስከማለት መድረሱንም ነው የጠቆሙት።
ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ የግንባታ ሥራ ለመጀመር ከኮንትራቱ ውጪ 1 ቢሊየን ዩሮ መከፈሉንም በመጥቀስ።
የተረከብናት ኢትዮጵያ 130 ሚሊየን ሕዝብ፣ ሰፊ የቆዳ ስፋት ያላት እና ብዙ ማምረት የምትችል ሀገር ብትሆንም በጂኦግራፊ የታሰረች መሆኗን መዘነጋት የለብንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።
“የጂኦግራፊ እስረኛ መሆን፣ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በልጆቻችን፣ በእነርሱ ልጆች ጭምር አደጋው እያደገ የሚመጣ ጉዳይ ነው” ሲሉም አክለዋል።
መንግሥት እያለ ሌላ መንግሥት እንዲያዝዛቸው የሚጠብቁ ተቋማት፣ በርካታ አሳሪ ሕጎች፣ በአጠቃላይ የሚዲያም የፖሊቲካ አውዱም የተሳከረ ነበር፤ ከፋፋይ እና በታኝ ትርክትም ፈተና እንደነበር መዘነጋት አይገባም በማለት ነው የነበረውን ሁኔታ ያብራሩት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰባት ዓመት በፊት የነበረችውን ኢትዮጵያ ገጽታ ማጤን የተላለፉ ውሳኔዎች ትሩፋትን በቅጡ ለመረዳት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢቢሲ
More Stories
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የተገቡ ቃሎች አንድ በአንድ እየተተገበሩ ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ታላቁን የክብር ኒሻን ለቢል ጌትስ ሸለሙ