ማሻ ፣ የግንቦት 27፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በፓርላማ ንግግር የተገቡት ቃሎች አንድ በአንድ እየተተገበሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
“ኢትዮጵያ ውስጥ የመጣው ለውጥ በባሕር ላይ እንደመሄድ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሂደቱ ግን ወጀብ መኖሩን ካላስታወሱ በጉዞው ላይ ፈተና እንደሚከብድ ጠቅሰዋል።
ለውጡ ሲመጣም ከሁሉም አቅጣጫ ወጀብ መኖሩን የዘነጋ ድጋፍ ከየአቅጣጫው አግኝቶ የነበረ መሆኑን አስታውሰው፣ እኛ ግን ስንነሣ ወጀብ መኖሩን አስበን ለሚገጥመን ፈተና ተዘጋጅተን ነበር ብለዋል።
መንግሥታቸው እየሠራቸው ያሉት ሥራዎች መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በፓርላማ ንግግር የተገባውን ቃል እንደሆነ ጠቅሰው፣ ሌሎች ግን ንግግሩን የሰሙት በትክክለኛ አውዱ ሳይሆን ለራሳቸው በተረጎሙት መልኩ ስለሆነ ወጀቡ ሲነሣ ግርታ ውስጥ እንደገቡ ገልፀዋል።
በዚህም ምክንያት እነዚህ በተሳሳተ ስሌት የተጓዙ ቡድኖች ራሳቸው ላይም ሆነ ሀገር ላይ ፈተና መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ኢቢሲ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።