ማሻ ፣ የግንቦት 17፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ ተናገሩ።
አብዛኛውን ጊዜ ፈተና ሲነሳ የፈተና ስርቆትና ኩረጃ አብሮ የሚነሳ ሲሆን፤ ይህን ለማስቀረት መንግስት ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የ12ኛ ክፍል ሀገረ አቀፍ ፈተናን ተማሪዎች ከተማሩበት ት/ቤት ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንዲፈተኑ አድርጓል።
ለፈተና ስረቆትና ኩረጃ የሚያግዙ ድምፅን ምስልን የሚወስዱ ማንኛውንም መሳሪያዎችን ተማሪዎች እንዳይጠቀሙና ይዘውም እንዳይገኙ በመከልከል፤ ጥብቅ ፈተሻ እንደሚደረገ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ተይዘው ሲገኙም እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ተማሪዎች ፈተናን ለመስረቅና ለመኮረጅ የሚያባክኑትን ጊዜ ትምህርቱን በሚገባ ቢያጠኑበት መልካም ነው፤ ውጤታማም ብለዋል።
በብይነ-መረብና በወረቀት የሚሰጠው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ መንገድ ለመስጠት፤ የትምህርት ተቋማት የቁሳቁስና የተለያዩ ዝግጅቶችን አጠናቀው ተማሪዎችን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ፈተናውን በብይነ መረብ የሚፈተኑ ተማሪዎች በየትምህርተ ቤታቸው ልምምድ በማድረግ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ዶ/ር እሸቱ፤ ፈተናውን በወረቀት የሚፈተኑ ተማሪዎችም ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያገኙ እየተደረገም ይገኛል ነው ያሉት።
ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ግብአቶች ዝግጁ መሆናቸውን መፈተሸና ለሰው ሀይል ስልጠናዎችን መስጠት፤ እንዲሁም ከክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮችና ከዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኢቢሲ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።