ማሻ ፣ የመጋቢት 26፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የቻይና ሲቪል አቪዬሽን ተቋም በዓለማችን የመጀመሪያው አብራሪ አልባ የአየር ታክሲ ትራንስፖርት በሃገሪቱ እንዲተገበር ፍቃድ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
በተቋሙ ፍቃድ የተሰጣቸው ኢ ሃንግ ሆልዲንግ እና ሄፊ ሄይ የተባሉት የአየር መንገድ ድርጅቶች ያቀረቡት ቴክኖሎጂ የአየር ላይ ታክሲን ሰው አልባ በሆነ መንገድ ወይም ያለአብራሪ መተግበር የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ራሱን የቻለ የአየር ተሽከርካሪ ወይም ሰው አልባ የመንገደኛ አውሮፕላን የሚል ስያሜ የተሰጠው ቴክኖሎጂው፤ በተገጠመለት የቦርድ ኮምፒዩተር፣ ጂፒኤስ፣ የሪሞት ኮንትሮል እና በሌሎች መሳሪያዎች እንደሚታገዝ ተመላክቷል፡፡
ስሪቱ ቱሪዝም ተኮር እና አጭር ርቀት በሆነ የሙከራ በረራ እንደሚተገበርም ነው የተገለፀው፡፡
ቻይና ከመሬት 1 ሺህ ሜትር ከፍታ ላይ የሚበሩ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን በመተግበር በዘርፉ የበላይነት ለመያዝ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑ ተነግሯል፡፡
ሃገሪቱ በፈርንጆቹ 2025 የመጨረሻ ዓመት በዘርፉ የሚንቀሳቀሰውን ገንዘብ 207 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እና በ2035 ደግሞ በእጥፍ ለማሳደግ እንደምትሰራም ኒውስዊክ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ኢቢሲ
More Stories
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ክንፍ፤ የቢሾፍቱ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በቻይና የተሰራው የዓለማችን ግዙፉ የጭነት ድሮን
በፀሐይ ኃይል የሚሠራው አነስተኛ ትራክተር ለማላዊ አርሶ አደሮች አዲስ ተስፋን ይዞ መጥቷል