በጉባኤው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የልማት ማህበሩ የበላይ ጠባቂ አቶ አበበ ማሞ እንደገለፁት በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር ግንቦት 16/1985 ዓ.ም ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ ህብረተሰቡን፣ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማስተባበር የዞኑን የልማት ፍላጎት የመደገፍ ስራዎች በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበሩ በእስካሁን ጉዞው በጤና ፣ በትምህርት ፣በመንገድ ግንባታ ፣ በባህል ዘርፍ ፣ በስራ ዕድል ፈጠራና በስልጠናና አቅም ግንባታ ለዞኑ ህዝብ በርካታ ተግባራትን ማበርከቱን ተናግረው ለቀጣይ የዘርፉ እንቅስቃሴ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ማህበሩ ከተቋቋመበት ዓላማና ካስቆጠረው ዕድሜ አንፃር ያስመዘገበው ውጤት በቂ ያለመሆኑን ገልፀው በቀጣይ ለሚሰሩ ተግባራት የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ አበበ አክለው ማህበሩ የላቀ አፈፃፀም እንዲያስመዘግብ ብቃት ያላቸውን የቦርድ አባላት በመምረጥ በመደማመጥና በጋራ መስራት ዋነኛው ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታፈሰ ደቁሾ የሸካ ህዝቦች ልማት ማህበር የዞኑን የልማት ፍላጎት የመደገፍ ስራዎች በመስራት ለበርካታ ዓመታት እያገለገለ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው ከህዝቡ የልማት ፍላጎት አንፃር አሁንም ቀሪ ተግባራት አሉበት ብለዋል።
የልማት ማህበሩን አቅም ለመገንባት ተጋግዞና ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ቦርድ ሰብሳቢው ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር በጋራ መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ዞኑ የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት መሆኑን የገለጹት አቶ ታፈሰ ፀጋዎችን ወደ ኢኮኖሚ በመቀየር ለጋራ ተግባር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በጉባኤው የልማት ማህበሩ የ32 አመት የጉዞ ትውስታ እና የእስካሁን የስራ ጉዞን የሚያሳይ የፎቶ ኤግዚቢሽን የቀረበ ሲሆን በቀጣይ የስራ ዕቅዶች ላይ ሪፖርት ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ውይይት ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።
በጉባኤው ላይ የሸካ ንጉስ ቴቺ ቄጆቺ ከነ ካቢኔያቸው ፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር ስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የኃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ
More Stories
የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
700 ሱቆችን በአንድ ጣራ ስር የያዘው የዓለማችን ግዙፉ የገበያ ማዕከል
ዓለምን ያስደመመው ኢትዮጵያዊ ዲዛይነር