በየማሻ ከተማ አስተዳደር በመልካም አስተዳደርና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች ዙሪያ የህዝብ አቀፍ ውይይት መድረክ በማሻ ከተማ ማካሄድ ጀምረዋል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሠራዊት አየነው እንደገለጹት እንድህ ዓይነት መድረክ ለቀጣይ ስራዎች አጋጅ በመሆኑ እስከአሁን ድረስ የተከናወኑ ስራን በጋራ በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል።
የከተማን ዕድገት ለማፋጠን የህዝቡ ድጋፍ በእጅግ ስለሚያስፈልግ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር በጉለቶች በታዩት ላይ የጋራ ርብርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አቶ ሰራዊት ተናግረዋል።
የማሻ ከተማ ማህበረሰብ ለከተማ ዕድገት በሁሉም ዘርፍ ድጋፍ ከማድረግ ወደ ኃላ ብሎ የማያውቅ ህዝብ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሠራዊት አሁንም ቢሆን የተለመደውን ትብብር በገንዘብ በጉልበትና በሐሳብ ከመንግስት ጎን እንድቆሙ ጠይቀዋል።
በቀጣይ ተግባራቶቻችን ላይ የህዝቡ ዕገዛ በእጅጉ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የመድረጉ ተሳታፊዎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን እንድቆም ከንቲባው ጥሪውን አስተላልፏል።
ዘጋቢ ካሳሁን ደንበሎ
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።