ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ “የ#አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል በማለት ገልጸው፤ የኅብረተሰቡ የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ መሆኑንም አመልክተዋል።
ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለናል፤ በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነውም ብለዋል።
ከሐረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦች አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን ማካፈላቸውንም በፅሁፋቸው አስፍረዋል፡፡
በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፡፡
FBC
More Stories
የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል – የትምህርት ፈተናና ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
የ2017 የፈተና አስተዳደር ስረዓት ዉጤታማ ለማድረግ በየደረጃዉ ያሉ አካላት ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር ይገባቸዋል ተባለ።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማትና በኮንስትራክሽን በርካታ የሥራ ዕድል እየፈጠረች ነው።