በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 490 ጋላክሲ ሳምሰንግ ሞባይል ስልኮች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ፖሊስ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል በአንድ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ ስልኮቹን መያዝ መቻሉ ተመላክቷል፡፡
የንግድ ምልክታቸው ጋላክሲ ሳምሰንግ የሆኑ እነዚህ 490 ሞባይል ስልኮች በሶስት ካርቶን ተደብቀው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ህጋዊነትን ያልተከተለ የንግድ አሰራር በሀገር ላይ የሚያስከትለው ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እና በህጋዊ ነጋዴው ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ እንደሆነ በመገንዘብ በህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ጤናማ የንግድ ውድድር እንዳይኖር የሚያደርጉ ግለሰቦች ሲያጋጥሙ ህብረተሰቡ ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት ለፀጥታ አካሉ እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
FBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ