ክሪስታል ፓላስ ራዮ ቫይካኖን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ውድድር ዋንጫን አንስቷል።
በሬድ ቡል አሬና በተደረገው የኮንፍረንስ ሊግ ፍጻሜ ፓላስ በጃን ፍሊፕ ማቴታ ብቸኛ ግብ የስፔኑን ተወካይ ራዮ ቫይካኖን አሸንፏል።
በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከፓላስ ጋር እንደሚለያዩ የሚጠበቀው አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር በለንደን ቆይተቻው ክለቡን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሁለት ትልልቅ ዋንጫዎች ባለቤት አድርገውታል።
ክሪስታል ፓላስ በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ መድረክ በተሳተፈበት ዓመት ነው የመጀመሪያውን የአውሮፓ ውድድር ዋንጫ ማሳካት የቻለው።
አሰልጣኙ በአንድ ዓመት ውስጥ የኮሙኒቲ ሽልድ ዋንጫን ጨምሮ 3ኛ ዋንጫቸውንም ያሳኩበት ሆኗል።
More Stories
ኢትዮጵያ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ሆነች
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
ተንሃም ወይስ ዌስትሃም – ከሊጉ ማን ይወርዳል