May 24, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ተንሃም ወይስ ዌስትሃም – ከሊጉ ማን ይወርዳል

ማሻ፤ ግንቦት 16/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የ2025/26 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዓመት ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍጻሜውን ያገኛል፡፡

በዛሬ ዕለት ወልቭስ እና በርንሌይን ተከትሎ ወደ ሻምፒዮንሺፕ የሚወርደው ሦስተኛ ቡድን የሚለይባቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ የሚመራው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ኤቨርተንን ያስተናግዳል፡፡

ከፈረንጆቹ 1977 በኋላ ከእንግሊዝ ዋናው ሊግ የመውረድ ስጋት ያለበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከጨዋታው አንድ ነጥብ የሚያገኝ ከሆነ በሊጉ መቆየቱን ያረጋግጣል፡፡

ሌላኛው የለንደን ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ ወደ ሻምፒዮንሺፕ የመውረድ ስጋት ያለበት ሲሆን፥ በሜዳው ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ይፋለማል፡፡

ዌስትሃም ዩናይትድ በሊጉ ለመቆየት የራሱን ጨዋታ አሸንፎ የቶተንሃም ሆትስፐርን መሸነፍ ይጠብቃል።