May 24, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ሆነች

ማሻ፤ ግንቦት 16/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሞዛምቢክ በመለያ ምት ተሸንፎ ከኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውጪ ሆኗል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በመደበኛው 90 ደቂቃ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጠናቅቀው ወደ መለያ ምት ያመሩ ሲሆን በዚህም ሞዛምቢክ በመለያ ምት 5 ለ 4 አሸንፋ ለአለም ዋንጫው አልፋለች፡፡