May 9, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አልጄሪያ እና ቡርኪና ፋሶ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

ማሻ፣ ታህሳስ 22/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አልጄሪያ እና ቡርኪና ፋሶ አሸንፈዋል።

በምድብ አምስት ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ በአልጀሪያ ኢኳቶሪያል ጊኒን 3 ለ 1 አሸንፋለች።

የአልጀኢሪያን የማሸነፊያ ግቦች ኢብራሂም ማዛ፣ ፋሬስ ቻይቢ እና ዚነዲን ቤላይድ ሲያስቆጥሩ ኤሚሊዮ ንሱ የኢኳቶሪያል ጊኒን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል።

እንዲሁም በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው ጨዋታ ቡርኪና ፋሶ ሱዳንን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችላለች።

በጨዋታው ላሲና ትራኦሬ እና አርሴን ኩዋሲ የቡርኪናፋሶን ግቦች አስቆጥረዋል።

ምድቡን አልጄሪያ ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ ስታጠናቅቅ ቡርኪና ፋሶ በስድስት ነጥብ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።

ምሽት 4 ሰዓት ላይ የምድብ ስድስት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ጋቦን ከኮትዲቯር እንዲሁም ሞዛምቢክ ከካሜሩን ይጫወታሉ።