ማሻ፣ ታህሳስ 25/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሱዳንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሴኔጋል ፓፔ ጉዬ (ሁለት) እና ምባዬ ባስቆጠሯቸው ሶስት ግቦች ሱዳንን አሸንፋለች።
ሱዳን ከሽንፈት ያልታደጋትን ብቸኛ ግብ አሚር አብደላህ ከመረብ አሳርፏል።
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ ማሊ እና ቱኒዚያ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
More Stories
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ
ኬንያዊው አትሌት በሽልማት ተንበሸበሸ