ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) በትራፊክ መጨናነቅ ምክንያት በረራ ያመለጣት ህንዳዊት ለበርካቶች ህይወት መጥፋት ምክንያት ከሆነው አደጋ 10 ደቂቃዎችን በመዘግየቷ መትረፏን ኤንዲ ቲቪ ዘግቧል።
ከባለቤቷ ጋር በለንደን ከተማ የምትኖረውና ከአደጋው በኋላ ከኤንዲ ቲቪ ጋር ቃለምልልስ ያደረገችው ቦሆሚ ቻውሃን የእረፍት ጊዜዋን አህመዳባድ ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር አሳልፋ በበረራ ቁጥር 171 ለመብረር ትኬት ቆርጣ ነበር።
ሆኖም ወደ አውሮፕላን ማረፊያው እያመራች በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳጋጠማት እና አስር ደቂቃ ዘግይታ አህመዳባድ አየር ማረፊያ ስትደርስ ግን ወደውስጥ እንዳትገባ በመከልከሏ መናደዷን ገልፃለች።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም እዛው አየር መንገዱ ውስጥ እያለች ወደለንደን ልትጓዝበት የነበረው አውሮፕላን መከስከሱን ማየቷን ተናግራለች።
ኢቢሲ
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች