ማሻ ፣ የሰኔ 06፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) ቻይና ከ53 የአፍሪካ ሀገራት የምታስገባቸውን ምርቶች ከቀረጥ ሙሉ በሙሉ ነጻ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በቻይና-አፍሪካ ስብሳባ ላይ አስታውቃለች።
ከዚህ ቀደም የቻይና የቀረጥ ነጻ እድል ተጠቃሚ የነበሩት 33 የአፍሪካ ሀገራት ብቻ እንደነበሩ ይታወሳል።
የአፍሪካ ሀገራት ወደ አሜሪካ በሚልኳቸው ምርቶች ላይ የቀረጥ ጭማሪ ሊያጋጥማቸው ይችላል በተባለባት በዚህ ወቅት፣ ቻይና ይህን ውሳኔ ማሳለፏ ለአፍሪካ ሀገራት አማራጭ የሚሰጥ እድል እንደሆነ ተነግሯል፡፡
አፍሪካዊቷ ሀገር ኢስዋቲኒ ቻይና የግዛቷ አካል አድርጋ የምትቆጥራትን ታይዋንን ነጻ ሀገር አድርጋ ዕውቅና በመስጠቷ ከዚህ እድል ተጠቃሚ እንደማትሆን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡
ቻይና ላለፉት 15 ዓመታት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛዋ የንግድ አጋር ሆና ቆይታለች፡፡
እ.አ.አ በ2023 ከአፍሪካ ሀገራት ወደ ቻይና 170 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ተልከዋል።
ኢቢሲ
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች