May 17, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል

ማሻ ፣ የግንቦት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ‘ኢቴኤክስ 2025’ ከዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ያዘጋጁት ይህ ኤክስፖ፤ የሳይበር ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ፋይን ቴክ፣ ስማርት ሲቲ እና የቴክኖሎጂ ትምህርትን መሰረት ያደረገ አምስት የትኩረት መስኮችን የያዘ ነው ተብሏል።

በቴክኖሎጂው ዘርፍ እንደ ሀገር የተሠሩ ስራዎችን ለዓለም ለማሳየት እና በቀጣይ መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ አቅምን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነም ተገልጿል።

የሦስት ቀናት ቆይታ በሚኖረው ኤክስፖው ላይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሮቦቲክስ ውድድሮች፣ ዐውደ ርዕዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ አቅምን የሚፈጥሩ በርካታ የጎንዮሽ ውይይቶች እንደሚደረጉም ተመላክቷል።

ከግንቦት 8 እስከ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው ኤክስፖ ከ10 ሺህ በላይ ታዳሚዎች እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

ፋና