ማሻ፤ ጥር 20/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የ2018 ዓ/ም የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ የተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ መኤኒት ጎልዲያ ወረዳ እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ እየተከሰተ ያለዉን የመሬትና የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የመሬት ፣ የውሃና የሰው ሀብት መጠበቅ ፣ ማልማትና በላቀ ደረጃ በማቀናጀት ጥቅም ላይ ማዋል ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መኾኑ ነዉ።
የ2018 የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ ዉጤታማ ለማድረግ የቅድመ ዝግጀት ስራዎች ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት መከናወኑ ተገልጿል።
የ2018 ዓ.ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ትግበራ ከወትሮ በተለየ በልዩ በትኩረትና በከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ እየተከናወነ እንደሚገኝ ከክልሉ ግብርና ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በወረዳው ባኒ ቀበሌ፣ ሸዊ ንዑስ ተፋሰስ እየተካሄደ በሚገኘው ክልላዊ ማብሰሪያ ፕሮግራም የግብርና ሚኒስትር ተወካዮች፣ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት እየተሳተፉ ይገኛል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች