ማሻ ፣ የግንቦት 27፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) አላማ ተኮር ተግባቦት ለሀገር ግንባታ በሚል መርህ ቃል የኮሚኒኬሽንና የሚዲያ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ተጀምሯል።
የክልሉ ርዕስ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው የሀገርን ብልጽግና ለማሻገር በሚደርገው ርብርብ ሂደት የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሚና የጎላ መሆኑን ነው የጠቆሙት ።
የዜጎችንና የማህበረሰብን አመለካከት በመቀየሩ ረገድም ሚዲያ ትልቅ አቅም እንዳለው በማስገንዘብ።
ዘርፉ እነዚህን ተልዕኮዎችን በአግባቡ እንዲወጣ በጥብቅ ዲሲፒሊን መመራት እንዳለበት አስምረዋል።
ወቅቱ በኢ-ተገማች ሁኔታዎች ውስጥ መሆኑን ያስረዱት ርዕስ መስተዳድሩ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ይህንን ሁኔታ በመረዳት ወቅቱን የሚመጥን ተግባቦት ለመፍጠር እንድተጉ አሳስበዋል።
በክልሉ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች የአካባቢውን ፀጋዎችን ከማስተዋወቅ ባሻገር ውጤታማ ተሞክሮችን እንዲያጎሉ ጥሪ ቀርቧል።
ወንድሙ ካኪሎ
More Stories
በቻይና የተሰራው የዓለማችን ግዙፉ የጭነት ድሮን
በፀሐይ ኃይል የሚሠራው አነስተኛ ትራክተር ለማላዊ አርሶ አደሮች አዲስ ተስፋን ይዞ መጥቷል
የነዳጅ ዘመን እያበቃ ይሆን? በ2030 የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም በከፍተኛ ደረጃ ሊጨምር ነው