May 6, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የማህበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ የጎላበት ምህዳር ተፈጥሯል- የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ።

ማሻ ፣ የግንቦት 27፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) አላማ ተኮር ተግባቦት ለሀገር ግንባታ በሚል መርህ ቃል በቦንጋ ከተማ በተካሄደው የኮሚኒኬሽንና የሚዲያ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ ላይ ለቀጣይ ተልዕኮ አጋዥ የሆኑ አስተያየቶች ቀርበዋል።

የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊው አቶ የሺዋስ አለሙ ወቅቱ የማህበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ መልኩ እያደገ የመጣበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ይህንን ሁኔታ በመረዳት ወቅቱን የሚመጥን የተግባቦት ሥርዓት ሥርዓት ለመገንባት ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅበት ነው የቢሮ ሃላፊው ያሰመሩት።

የለውጡ መንግስት የመረጃ ነፃነትን የሚያረጋግጥ ምህዳር ፈጥሯል ያሉት አቶ የሺዋስ ወቅቱን የዋጀና የሀገርን ጥቅም የሚያስቀድም የኮሚኒኬሽን ስራ መጠናከር እንዳለበት በመድረኩ ተነስቷል ።

በክልሉ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት እና የኮሚኒኬሽን ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ፣እንዲሁም የማህበረሰብ አንቂዎች በተሳተፉበት በዚህ መድረክ ጠቃሚ ሀሳቦች ቀርበዋል።

ዘጋቢ ወንድሙ ካኪሎ