በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ዮክጪጪ ቀበሌ እየተሠራ ያለውን የገጠር ኮሪደር ልማት ስራን የዞኑ፣የ3ቱ ወረዳና የየወረዳው ቀበሌ አመራሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራን ፅንሰ ሃሳብ በተገቢው በመረዳት ለተግባራዊነቱ መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በአንድራቻ ወረዳ የዮክጪጪ ቀበሌ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ፅንሰ ሃሳብን በተገቢው የተረዳና ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ቀበሌ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አበበ ማሞ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ከአጥር በተጨማሪ የግቢ ውቤት በመጠበቅ ምቹ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሁም የተሟላ የሌማት ትሩፋት ስራን ያካተተና የተሻለ ገቢ ያለው ነዋሪን መፍጠር እንደሆነ አብራርተዋል።
በዮክጪጪ ቀበሌ የተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ሁሉን ያሟላ መሆኑን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው የ3ቱም ወረዳ ቀበሌዎች በተገቢው ተግባራዊ ልያደርጉ ይገባል ሲሉ ገልፀው የወረዳ መዋቅሮችም ለተፈፃሚነቱ ቅርብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በማለት አሳስበዋል።
ለጎብኚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአንድራቻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ አገሎ በወቅቱ እንደተናገሩት በወረዳው ከሚገኙ 17 ቀበሌዎች መካከል የዮክጪጪ ቀበሌ አንዱ መሆኑን ገልፀው ቀበሌው የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ፅንሰ ሃሳብን ቀድሞ በመረዳት ወደ ተግባር ገብቷል ብለዋል።
ከዮክጪጪ ቀበሌ በተጨማሪም የወረዳው ሁሉም ቀበሌዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ በልዩ ትኩረት እየተሠራ ይገኛል ሲሉ አክለዋል አቶ አየለ።
በጉብኝቱ የተሳተፉት ከየወረዳው የመጡ የቀበሌ አመራሮች በወቅቱ እንደገለፁት በዮክጪጪ ቀበሌ ባዩት ነገር መደነቃቸውን ገልፀው ይህንን ተሞክሮ በቀበሌያቸን በመውሰድ ተግባራዊ እናደርጋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ከየወረዳው የመጡ አመራሮች በበኩላቸው የዮክጪጪ ቀበሌን ተሞክሮ በመውሰድ ቀበሌዎችን በሙሉ ሞዴል ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል።
ከጉብኝቱ በኋላ በቀጣይ በዞኑ ሁሉም የወረዳ ቀበሌዎች የገጠር ኮሪደር ልማት ስራን ማሳካት በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች