August 12, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የጋራ ትጋት ለትምህርት ልማት እምርታ!” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2019 ዓ ም ትምህርት ልማት ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በማሻ ከተማ ተካሂዷል።

የትምህርት ስራን በትጋት መደገፍና የዲጂታል ዘመንን ማጠናከር ለሀገር የሚተርፍ ትውልድ ለማፍራት ሚናው የጎላ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፤

‎‎”የጋራ ትጋት ለትምህርት ልማት እምርታ!” በሚል መሪ ቃል በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2019 ዓ.ም ትምህርት ልማት ስራዎች ንቅናቄን በማሻ ከተማ አካሂዷል።

‎መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች አንዱ ትምህርት ነው፡፡ በእውቀት የታነጸና በስነምግባር ተመሰገነ ሀገር ወዳድ ትልድ ለማፍራት ትምህርት ጥራት ላይ መስራት ከሀገር ወዳድ ዜጎች ይጠበቃል፡፡

ይህንኑ ዓለማ ለማሳካት ያለመ የውይይት መድረክ በማሻ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ‎የማሻ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማንደፍሮ እንደሻው ባለፈው የትምህርት ዘመን የተመዘገበውን ጠንካራ ጎን በማስቀጥል በጉለቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መምከር አስፈለጊ መሆኑን ተከትሎ መድረኩ እንደተዘጋጀ አብራርተዋል፡፡

‎ከመንግስት በተጨማሪ በግል ትምህርት ቤት ከፍተው ትውልድ የሚያንጹ ተቋማትን የግብዓት እጥረት በመቅረፍ ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግም ኃላፊው አውስተዋል፡፡

በመንግስትም ይሁን በግል ትምህርት ቤቶች ላይ በቂ የሰው ኃይልና መርጃ መሳሪያ መኖሩን ማረጋገጥ የመንግሰት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ያስታወሱት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዳዷለም ጌታቸው ከወላጅ ጀምሮ የሚመለከታቸው ሁሉ ከእኔ ይልቅ የኛ በሚል አስተሳሰብ የትምህርት ስራን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ከወረቀት ንክኪ ነጻ ››የኦን ላይን›› ፈተና በከተማ ደረጃ ያለምንም ችግር ማስፈተን መቻሉን የተናገሩት የውይይቱ ተሳታፊዎች ስኬቱ የጋራ በመሆኑ ለተፈታኞች መልካም ውጤት እንዲሆን እንመኛለንም ብለዋል፡፡

በትምህርት ረገድ እየመጣ ያለውን ውጤት የበለጠ ለማሳደግ ትምህርት ቤቶችን በግብዓት የማደራጀት ስራ ከመስራት አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት ያመላከቱት የውይይቱ ተሳታፊዎች በግለሰብ ደረጃ የሚጠበቅብንን እንወጣለን ብለዋል፡፡