ማሻ ፣ የግንቦት 08፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያው ቲክቶክ የአውሮፓ ህብረትን የዲጂታል አገልግሎት ሕግ ጥሷል በሚል ክስ ቀርቦበታል።
በዚህ ክስ የቲክቶክ ባለቤት ባይትዳንስ ከዓለም አቀፍ ገቢው እስከ 6 በመቶ የሚደርስ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት ሥራ አስፈፃሚ፥ ቲክቶክ ተጠቃሚዎቹ የማጭበርበሪያ ማስታወቂያዎችን ለይተው እንዲያውቁ የሚያስችላቸውን የዲጂታል አገልግሎት ሕግ ማክበር አልቻለም ብሏል።
በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ቲክቶክ ለማስታወቂያ ለማን እንደሚከፍል፣ ማስታወቂያው ማን ላይ እንደሚያነጣጥር እና ማስታወቂያዎቹ ምን እንደያዙ በግልፅ እያሳየ አለመሆኑን ገልጿል።
በሌላ በኩል ክስ የቀረበበት ቲክቶክ የአውሮፓ ህብረት የዲጂታል አገልግሎት ሕግን የተረዳበትን መንገድ አልደግፍም ሲል ተቃውሟል።
ቲክቶክ መተግበሪያውን ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ግልፅ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል::
የማስታወቂያ አሠራሩን ለሕዝብ ክፍት ለማድረግም በንቃት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
ኢቢሲ
More Stories
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ክንፍ፤ የቢሾፍቱ ግዙፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትራቴጂካዊ ፋይዳ
በቻይና የተሰራው የዓለማችን ግዙፉ የጭነት ድሮን
በፀሐይ ኃይል የሚሠራው አነስተኛ ትራክተር ለማላዊ አርሶ አደሮች አዲስ ተስፋን ይዞ መጥቷል