የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ መሆኑን ፎርብስ ይፋ አድርጓል፡፡
ፎርብስ መጽሔት በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት÷ ሪያል ማድሪድ በ9 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ዋጋ የዓለማችን ውዱ ክለብ መሆን ችሏል፡፡
ሪያል ማድሪድ በውድድር ዓመቱ ስኬታማ ጊዜ ባያሳልፍም ለተከታታይ አምስተኛ ዓመት የዓለማችን ውዱ ክለብ በመሆን በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡
ሌላኛው የስፔን ክለብ ባርሴሎና በ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር 2ኛ ሲሆን÷ ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ በ7 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በተጨማሪም ሊቨርፑል በ6 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር እና ፒኤስጂ በ5 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ዋጋ በተከታታይ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ አርሰናል በ5 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በመጨረሻ ሳምንት በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው ቶተንሃም ሆትስፐር በበኩሉ በ3 ቢሊየን ዶላር ዋጋ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
More Stories
ፒኤስጂ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!
ኢትዮጵያ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ሆነች