May 22, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

‎ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ለሀገር በቀል ዕውቀቶች ትኩረት ተሰጥቷል፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶር)

‎ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በተገኙበት ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሠልፍ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ተካሂደዋል ።

‎የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ብልፅግና ፓርቲ አካታች የሆነውን የፖለቲካ ስረዓት በመገንባት ሀገር በቀል ዕሳቤ በሆነው መደመር የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየመለሰ የመጣ ነው ብለዋል።

‎ዞኑ ለልማትና ኢንቨስትመንት ምቹ ስነምህዳር ያለው መሆኑን ገልፀው በሀገር በቀል ዕሳቤ ሠላሙን መገንባት በመቻሉ የልማቱ ተጠቃሚ መሆን ችሏል ነው ያሉት።

‎ከመንግስት ተቋማት ጎን የባህላዊ አስተዳደር ሚና የጎላ መሆኑን ተናግረው ይህም የለውጡ መንግስት ቱሩፋቶች ናቸው ብለዋል።

‎በሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በማድረግ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ያሻሻሉና ክልሉ በራስ አቅም 60 በመቶ የምሆነውን በጀት መሸፈን መቻሉን ተናግረዋል።

‎ርዕሰ መስተዳደሩ አክለው ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ አካባቢውን የኢኮኖሚና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ፓርቲው በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት ።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን በሸካ ዞን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ተዋደውና ተከባብረው በህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚኖርበት መሆኑን አስታውሰዋል ።

‎በለውጡ ሀገርቷን ከነበረችበት ውስብስብ ችግሮች በማላቀቀ በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል ።

‎ፓርቲው ለዘመናት ተዘንግቶ የነበሩትን አካባቢዎች ትኩረት በመስጠት የመሠረተ ልማት ግንባዎችን እየተካሄደ መሆኑን ገልፀው በተቋም ግንባታ ረገድ በተከናወነ ስራም የድጂታል 2025ን በማሳካት 2030 ውጤታማ ለመሆን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።

‎ኃላፊው አክለው ፓርቲው ሀገርቷ በኢ-ፍትሀዊ አካሄድ ያጣችውን የባህር በር ጥያቄ ለማስመለስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በ7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፓርቲው አብላጫ ድምፅ እንድያገኝ ለአባሉና ደጋፊው ጥሪ አቅርበዋል ።

‎የሸካ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አበበ ማሞ እንደተናገሩት ብልፅግና በኢትዮጵያ ታርክ ውስጥ ሪፎርም በማድረግ የመጣና ትላንትን በማከም ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማፀናት እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

‎ፓርቲው የማህበረሰብ የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሆነው በክልል የመደራጀት መብት የመለሰና ፍታሀዊነትን ለማስፈን ቴፒን የብዘሀ ማዕከል ከተሞች አንዷ እንድትሆን ተደርጓል ነው ያሉት።

‎ዞኑ ከፍተኛ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገቢያ የሚያቀርብ መሆኑን ገልፀው በዚህም የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሴርትፍኬሽን ማዕከል ወደ ስራ እንድገባ መደረጉን ተናግረዋል ።

‎በማህበራዊው ዘርፍ በጤናው መስክ ይስተዋሉ የነበረውን የሆስፒታል እጥረት ለመፍታት ግንባታዎች ተከናውኗልም ብለዋል