May 19, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአመጋገብ ሥርዓታችንን ለመቀየር የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ተጠናክሮ ይቀጥላል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2018 (ኢዜአ)፡- እንደ ሀገር የአመጋገብ ሥርዓታችንን ከመሰረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስታወቁ።

የከተማ ነዋሪዎችን የኑሮ ዘይቤ ለመቀየርና የምርት ባህልን ለማሳደግ የሌማት ትሩፋት ትልቅ አስተዋጽዖ አለው ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በሐረር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን የማር፣ የወተትና የዶሮ እርባታ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን መጎብኘታቸውንም አስታውቀዋል።

በከተማው በኢኒሼቲቩ በግለሰብና በመንግሥት ደረጃ ሼዶችን በመገንባት የማር፣ የወተት፣ የእንቁላልና የዓሣ መንደሮችን የማቋቋም ሥራ በስፋት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ሀገር የአመጋገብ ሥርዓታችንን ከመሰረቱ ለመቀየር እና በምግብ እራስን ለመቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ሲሉም አመላክተዋል።

የእንስሳት፣ የዶሮና ዓሣ ዝርያ ማሻሻልና መኖ ማቀነባበሪያዎች ላይም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት እንደሚገኝ ነው ያስታወቁት።