May 13, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ማንቼስተር ሲቲን በዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚያቆየው ወሳኝ ጨዋታ…

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በኢቲሃድ ስታዲየም ከክሪስታል ፓላስ ጋር የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ምሽት አራት ሰዓት ላይ በሚካሄደው በዚህ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት ግጥሚያውን ማሸነፍ ይጠበቅበታል፡፡

ሲቲ የምሽቱን ጨዋታ ከተሸነፈ ወይም አቻ ከወጣ እንዲሁም አርሰናል በመጪው ሰኞ ከሊጉ መውረዱን ካረጋገጠው በርንሌይ የሚያደርገውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለ የ2025/26 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው ከመሪው አርሰናል በአምስት ነጥብ አንሶ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ÷ የምሽቱን ጨዋታ ካሸነፈ ልዩነቱን ወደ ሁለት በማጠበብ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚቆይ ይሆናል፡፡

ሊጉን አርሰናል በ79 ነጥብ እየመራ ሲሆን÷ ማንቼስተር ሲቲ በ74 ነጥብ፣ ማንቼስተር ዩናይትድ በ65 እንዲሁም ሊቨርፑል በ59 ነጥብ ከ2ኛ አስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ ይከተላሉ።