በኢራን ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ወታደራዊ ዘመቻ ቀስ በቀስ እየቀነሰ እንደሚሄድ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ምሽት ላይ በሰጡት መግለጫ÷ አሜሪካ የኢራንን የውጊያ አቅም በማዳከም ጦርነቱን ለማጠናቀቅ ማቀዷን ገልጸዋል።
አሜሪካ ዓላማዋን ለማሳካት ከጫፍ ደርሳለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሀገራቸው በኢራን ላይ የምታካሂደውን ዘመቻ ቀስ በቀስ ትቀንሳለች ብለዋል።
ነገር ግን አሜሪካ ዘመቻውን ስታካሂድ ሌሎች በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚጠቀሙ ሀገራት የመስመሩን ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
አሜሪካ ወደ ኢራን የምድር ጦር ለማሰማራት የሚያስችል ዝርዝር እቅድ እያወጣች እንደሆነ ጠቅሰው÷ ሀገራቸው የተኩስ አቁም ስምምነት የማድረግ ፍላጎት እንደሌላት ጠቁመዋል።
ጦርነቱ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ እያስከተለ ያለውን ጫና ለመቀነስ አሜሪካ በኢራን ነዳጅ ግብይት ላይ ጥላው የነበረውን ማዕቀብ በጊዜያዊነት ማንሳቷንም ይፋ አድርገዋል።
3ኛ ሳምንቱን በያዘው ጦርነት እስራኤል ትናንት ምሽት በቴህራን እና በሊባኖስ በርካታ የሚሳኤል ጥቃቶችን መፈጸሟን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰው ተቃውሞ ቡድን (ሂዝቦላህ) በወሰደው የአፀፋ ጥቃት በሰሜናዊ እስራኤል በሚገኘው የፋይለን የጦር ሰፈር ላይ ጥቃት መፈፀሙን የፕሬስ ቲቪ ዘገባ አመላክቷል፡፡
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች