ማሻ፤ መጋቢት 4/2018 ዓ/ም(ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የአሜሪካ ነዳጅ ጫኝ የጦር አውሮፕላን በምዕራባዊ ኢራቅ መከስከሱ ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካ ጦር ዲፓርትመንት እየበረሩ ላሉ ተዋጊ ጀቶች አየር ላይ ነዳጅ የሚሞላው “ኬሲ-135” አውሮፕላን መውደቁን በማረጋገጥ÷ አደጋው የተከሰተው በጠላት ወይም በወዳጅ ሀገር ተኩስ አይደለም ብሏል።
አደጋው ሁለት አውሮፕላኖች ላይ መከሰቱን ጠቅሶ÷ ነዳጅ መሙያ አውሮፕላኑ ሲከሰከስ ሌላኛው በሰላም መሬት ላይ ማረፉን ገልጿል፡፡
አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ምዕራባዊ ኢራቅ ውስጥ የነፍስ አድን ስራ እየተከናወነ መሆኑንም አመልክቷል።
አውሮፕላኑ ሲወቅድ በሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የተባለ ነገር የለም።
በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አምስት የአሜሪካ ወታደሮች በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙም የታወቀ ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።
የተከሰከሰው አውሮፕላን በጦርነቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለውና ተዋጊ ጀቶች እና ቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች ረጅም ርቀት ተጉዘው ዒላማዎችን በሚመቱበት ወቅት በቂ ነዳጅ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ተገልጿል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች