ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከኢፌዴሪ ግብርና ሚንስቴር ጋር በመተባበር ለገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ዙሪያ የተካሄደው የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል ።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን የዲጂታል ኢኮኖሚን እዉን ለማድረግ ባለፉት ዓመታት የተሳካ ስራ መሰራቱን ገልጸዉ 2030 የዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ለማሳካት ስራዎች እየተሰሩ መቆየቱን ገልፀዋል።
በመንግስትና በፓርቲዉ ከተያዙ ዕቅዶች አንዱ በሆነዉ የዲጂታል ፋይዳ ምዝገባ በተደረገዉ ርብርብ በክልሉ ለዉጦች መመዝገባቸዉን ገልፀዉ ሆኖም ከተቀመጠው ግብ አንፃር ዕቅዱን ለማሳካት የተጠናከረ ስራ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል ።
የዲጂታል ፋይዳ ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥ የገጠር ትራንስፎርሜሽን እዉን ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል ።
ለአርሶና አርብቶ አደሩ የፋይናንስ አገለግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ተናግዉ ስራዉን ይበልጥ ለማሳለጥ ግብረ-ሃይል በማደራጀት ተግባሩን መከታተልና መፈፀም እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።
የፋይናንስ ተደራሽነትን ለአርሶ አደሩ ለማድረስ የፋይዳ መታወቂያ ድርሻ የጎላ መሆኑን የተናገሩት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተደድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ በበኩላቸው ለስራዉ መሳካት የአመራሩ ድርሻ ከፍተኛ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።
ሁለተኛዉን የመሬት ልኬት ስራን ከዲጂታል ፋይዳ ጋር የማስተሳሰር ስራን አጠናክሮ ለማስቀጠል የግንዛቤ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገ ተናግረዋል።
ተመሳሳይ አረዳድ በመያዝ ወጥነት ያለዉን ስራ በታችኛዉ መዋቅር ድረስ በማዉረድ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ማስረሻ ለተግባሩ ስኬታማነት ሁሉም የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ አሳስበዋል ።
እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ለ398 ሺህ አርሶ እና አርብቶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ልኬት ስራን የማከናወን ሰራ እንደሚሰራ ጠቁመዉ ሰርተፍከሽን ያገኙ አርሶ አደሮችም የዲጂታል ፋይዳ አገለግሎት ተጠቃሚ በመሆን የዲጅታል ፋይናንስ እንዲያገኙ እንደሚሰራም አቶ ማስረሻ ተናግረዋል።
የዲጂታል ፋይዳ ተጠቃሚነት ይበልጥ በማረጋገጥ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ሥራን እዉን ማድረግ ይገባል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች