May 6, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሜሪካና የእስራኤል ጥምር ጦር በኢራን ባደረሰው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ወደ 787 ከፍ ማለቱ ተገለጸ፡፡

ማሻ፤ የካቲት 24/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) እስራኤል በኢራን ፕሬዝዳንታዊ ቢሮ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መሰንዘሯን አስታውቃለች፡፡

ተባብሶ በቀጠለው በዚህ ጥቃት ቴህራንን ጨምሮ በርካታ የኢራን ግዛቶች መትቻለሁ ብላለች እስራኤል፡፡

ቢቢሲ በበኩሉ ናታንዝ የተሰኘው የኢራን የኒኩሌር ጣቢያ መውደሙን አረጋገግጫለሁ ብሏል፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ቴላቪቭ ተጨማሪ ጥቃቶችን ለመሰንዘር በሊባኖስ ቁልፍ ስፍራዎችን እየያዘች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ የመልስ ምት የሚሆኑ በርካታ ጥቃቶችን መሰንዘሯን ስትቀጥል፤ 30 የሚሆኑ የጦር ሰፈሮችን ዒላማ አድርጊያለሁ ብላለች፡፡

በሪያድ ሳውዲ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በኢራን ሁለት ድሮኖች በደረሰበት ጥቃት መውደሙም ተነግሯል፡፡

እስራኤልና አሜሪካ በኢራን እስካሁን ባደረሱት ጥቃት የሟች ቁጥር ወደ 787 ከፍ ብሏል፡፡
በኩዌት ስድስት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውም ታውቋል፡፡

የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በፈጠረው ቀውስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል፡፡