ማሻ፤ ጥር 14/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) 2 ነጥብ 6 ሚሊየን ዓመታትን ያስቆጠረ እና ፓራንትሮፕስ የሚል ስያሜ ያለው የሰው ልጅ ዝርያ በአፋር ክልል ሚሌ ሎጊያ በተባለ ስፍራ ተገኝቷል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር በሰጡት መግለጫ፥ ባለስልጣኑ ከሚያከናውናቸው ሥራዎች አንዱ የሰው ልጅ ቅሪት አካላት ላይ ምርምር ማድረግ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ከውጭ ሀገራ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን ባደረጉት ጥናትና ምርምር አትዮጵያ የሰው ዘር መገኛነቷን በዓለም መድረክ አስተዋውቀዋል ነው ያሉት።
በዛሬው ዕለትም ከዚህ በፊት ያልታዬ የሰው ልጅ ዝርያ በአሜሪካ የችካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ በሆኑት ዘረሰናይ ዓለምሰገድ (ፕ/ር) በተመራ ልዑክ መገኘቱን ተናግረዋል።
ግኝቱ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን እና ለአንተሮፖሎጂ ምርምር ኢትዮጵያ እና የአፋር ክልል ተመራጭ መሆናቸውን የበለጠ የሚያረጋግጥ መሆኑን አመላክተዋል።
ግኝቱ በዓለም ላይ ታዋቂ በሆነው ኔቸር መጽሔት ላይ በዛሬው ዕለት እንደሚታተም ጠቁመዋል።
More Stories
በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ አዘጋጅነት የተካሄደው14ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ተጠናቀቀ ።
ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ውስጥ 21ሺ 5መቶ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ ምርት ጥራት ምርምርና ሰርትፍኬሽን ማዕከል አስታወቀ።
አሜሪካ ከኢራን ጋር ባደረገችው ጦርነት 25 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ አጣች